በኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም

አዲስ አባባ፣ ሀምሌ 20/2009 ዓ.ም – ማህበራችን ከሀምሌ 28 እስከ ነሐሴ 07/2009 ዓ.ም በእንግሊዝ ለንደን የሚካሄደውን 16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ምክንያት በማድረግ አባላቱ በወቅታዊ የአለም አትሌቲክስ ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለመጨመር የሚያስችል የአንድ ቀን የማነቃቂያ ስልጠና የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 22/2009 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ጀምሮ በኢንተርኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል እንዳዘጋጀ አስታውቋል፡፡

  ‹‹ እንደዚህ አይነት የአቅም ግምባታ ስልጠናዎች የማህበራችን አባላቶች ካላቸው እውቀት ባሻገር የተሻለ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ከማስቻላቸው በተጨማሪ ፤  እርስ በርስ መቀራረብን ፤ ልምድ እና ተሞክሮዎቻችን መለዋወጥን እና በጋራ ጉዳዮቻችን  ዙሪያ የመመካከር ባህልን ለማዳበር ይረዳሉ ብዬ አምናለሁ፡፡

 በመሆኑም አዲሱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደዚህ አይነት የአባላቱን ሙያዊ እድገት የሚያግዙ ተከታታይ የአቅም ግምባታ ስልጠናዎችን ከሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ የስፖርት አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር  ማዘጋጀቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡››  ሲሉ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ጋዜጠኛ ዮናስ ተሾመ የስልጠናውን መዘጋጀት አስመልክቶ ለድረ-ገጻችን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ESJA General Assembly, April 21, 2017
Photo by Demeke Feyisa

ስልጠናውን በአትሌቲክስ ስፖርት ዘገባዎች ላይ ከፍተኛ ልምድ ያካበተው የማህበራችን አባል  ጋዜጠኛ ፍቅር ይልቃል የሚሰጥ ሲሆን፣ በእለቱም ለስልጠናው ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት፣ የአዳዲስ አባላት ምዝገባ እና የሁላችንም ድምጽ እንዲሆን ታስቦ በማህበራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ይፋዊ ድረ-ገጽ  ምርቃት እና ሌሎች ዝግጅቶችም ይኖራሉ፡፡

 

 

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *