በ ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም – ቦነስአይረስ፡ መስከረም 26/2011 ዓ.ም

አራት ሽህ አትሌቶች፡ ከ206 ሀገራት በ32 የስፖርት አይነቶች ለ13 ቀናት፡ የአለምን ትኩረት በመሳብ አርጀንቲና በታሪኳ ያዘጋጀችው ትልቁን የስፖርት ውድድር ለማድመቅ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ይህችን ቀን ብቻ ይጠብቃሉ፡፡

እድሜያቸው ከ15 – 18 ብቻ የሆኑ ታዳጊዎች ያላቸውን እምቅ ስፖርታዊ ተሰጥኦ በለጋነታቸው አውጥተው ለአለም ለማሳየት ፡ ከምንም በላይ ደግሞ በኦሎምፒዝም ጽንሰ-ሀሳብ በስፖርት ጤናማ እዕምሮ እና አካልን እየገነቡ ማደግን: በውደድሩ አማካኝነት ከመላው አለም ተሰባስበው በአንድ የኦሊምፒክ መንደር በሚኖሩበት ወቅትም በሰላም አብሮ የመኖርን፡ የባህል እና የእውቀት ልውውጥን እንዲማሩበት ለማድረግ ታስቦ እ.ኤ.አ 2010 በሲንጋፖር መከናወን የጀመረው ይሄው የታዳጊዎች ኦሊምፒክ ከአራት አመት በፊት ናንጅንግ ቻይና ሁለት ብሎ ዘንድሮ አርጀንቲና ላይ ደርሷል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት የታዳጊ ኦሊምፒኮች ላይ ከመሳተፍ ባለፈ በወቅቱ ተስፋ እንዲጣልባቸው ማድረግ የቻሉ እና በጊዜ ሂደትም ውጤታማ የሆኑ እንደ ዮሚፍ ቀጀልቻ አይነት ስፖርተኞችን የተመለከተችበት ውድድር ሲሆን፡ ዘንድሮም ምንም እንኳን በቁጥር አነስ ያሉ አትሌቶችን ይዛ ብትቀርብም ካለፉት ውድድሮች የተሻለ ውጤት ለማምጣት ጠንክራ ስትሰራ መክረሟን ከቡድኑ መሪ እና አሰልጣኞቹ ማወቅ ተችሏል፡፡

✍ የሶስተኛው የታዳጊ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ልኡካን

1. አቶ ታምራት በቀለ – የቡድን መሪ
2. አብርሃም ኃ/ማርያም – የአትሌቲክስ ዋና አሰልጣኝ
3. ገብረሚካኤል ተክላይ – የአትሌቲክስ ም/አሰልጣኝ
4. ተከስተ ጥላሁን – የብስክሌት አሰልጣኝ

✍ ሴት አትሌቶች
5. አትሌት – አበራሽ ምንስዎ – 3000ሜ
6. >> – መቅደስ አበበ – 2000ሜ. መሠ
7. >> – ሒሩት መሸሻ – 800ሜ
8. >> – ስንታየሁ ማስሬ – 5000ሜ እርምጃ
9. >> – ለምለም ሀይሉ – 1509ሜ

✍ ወንድ አትሌቶች

10. አትሌት – በሪሁ አረጋዊ – 3000ሜ
11. >> – አብረሃም ስሜ – 2000ሜ. መሠ
12. >> – መለሰ ንብረት – 1500ሜ
13. >> – ጣሰው ያዳ – 800ሜ

✍ በባይስክል ውደድር ተሳታፊ አትሌቶች

14. ዛይድ ሀይሉ
15. ጻድቃን ገብረኪዳን

✍ ለ IOC ጉባኤ ተሳታፊነት

16. የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ
17. የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስራ አስፈጻሚ አባል ኮ/ል ደራርቱ ቱሉ

ዛሬ ወደ ቦነስ አይረስ ከሚገባው የአትሌቲክስ ቡድን ውጭ የተቀሩት የልኡኩ አባላት ከረቡዕ ጀምረው አርጀንቲና የደረሱ ሲሆን በኮታ ጥበት ምክንያት የአትሌቲክስ ቡድኑን ከሌሎች አጋሮቹ ጋር ከነሀሴ 14 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሰራ የነበረው አሰልጣኝ ብርሀኑ መኮነን ከሶስት ቀናት በፊት ከቡድኑ ጋር እንደማይጓዝ ተገልጾለታል፡ በሁኔታውም በእጅጉ ማዘኑን የገለጸ ሲሆን፡ የተቀሩት አሰልጣኞች ደግሞ እንደ ባለሞያ በዚህ ሰዓት በመቀነሱ ማዘን ብቻ ሳይሆን እነሱ ላይም ከፍተኛ የስራ ጫና እንደሚፈጥርባቸው ገልጸዋል፡፡

በዘንድሮው የታዳጊ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ከተፈጸሙ አስገራሚ ነገሮች መካከል :-

1. በኦሊምፒክ ውድድሮች ታሪክ የወንድ እና ሴት ተሳተፊ አትሌቶች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ስለሆነ

2. ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ የዛሬው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ስታዲየም ውስጥ ሳይሆን ሁሉም የቦነስአይረስ ህብረተሰብ ሊመለከተው በሚችልበት መልኩ በከተማዋ ዋና አደባባይ ላይ የሚከናወን መሆኑ

3. በ2020 የቶኪዮ አዋቂዎች ኦሊምፒክ ላይ ሊካተቱ ይችላሉ የተባሉ እንደ ድብልቅ ጾታን የሚያካትቱ የውድድር አይነቶች የሙከራ ውድድር የሚደረግበት መሆኑ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *