Haileegziabher Adhanom

በኦምና ታደለ

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር፣ ከአለምአቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር እና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር በትብብር ያዘጋጀው ስልጠና በሳምንቱ መጨረሻ ሚያዚያ 6 እና 7/2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዘማን ሆቴል ተካሂዷል፡፡ ስልጠናው በዋናነት በዘመናዊ የስፖርት ጋዜጠኛነት እና ፈተናዎቹ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡


በአዘማን ሆቴል የተካሄደውን ስልጠና የሰጡት የአለምአቀፉ የስፖርት ጋዜጨኞች ማህበር አስተማሪ እና ከ25 ዓመታት በላይ በስፖርት ጋዜጠኛነት ያሳለፉት ጣሊያናዊው ሪካርዶ ሮማኒ ሲሆኑ፡ ስልጠናው ጋዜጠኞች በዘመናዊው የሚዲያ አለም ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን በማመጣጠን እንዴት ማቅረብ እንደሚችሉ ተሞክሯቸውን በመጨመር ያካፈሉበት ነበር፡፡

በስልጠናው በተጨማሪም ጋዜጠኞች ለዜናዎች እና ትንታኔዎች በቂ ዝግጅት አድርጎ አግባብ የሆነ እና በፍሬ ነገር የተሞላ ዘገባ ማድረስ እንደሚቻል እንዲሁም በአንድ ግዜ ከአንድ በላይ ሙያዊ ክንዋኔዎችን እየሰሩ በዘመናዊው የሚዲያ አለም መላመድ እንደሚቻል ለማሳየት የተሞከረበት ስልጠና ለኢትዮጵያዊያን የስፖርት ጋዜጠኞች ተሰጥቷል፡፡ ሮማኒ በስልጠናው ላይ ዘመናዊ የስፖርት ጋዜጠኞች ከመፃፍ በዘለለ ፎቶዎች አና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ማንሳት እና ማረም ከጋዜጠኞች ዘመኑ የሚጠይቀው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የስፖርት ጋዜጠኝነት እና ስነ-ምግባር ሌላው በስልጠናው ላይ አፅኖት ተሰጥቶት ሰፊ ውይይት የተደረገበት ጉዳይ ነበር ፡፡ ስፖንሰርሺፕ፣ የፋይናንስ አቅም እና ፖለቲካ በብዛት ተፅዕኖ በሚያሳድሩበት የሚዲያ አለም ላይ የስፖርት ጋዜጠኞች ነፃ ለመሆን የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ላይ ስልጣና ተሰጥቷል፡፡
የአለምአቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር መሰል ስልጠና በኢትዮጵያ ሲሰጥ ይህ ለመጀመሪያ ሲሆን ፡ ቀጣይነት እንዲኖረውም በስልጠናው ተሳታፊ የነበሩ ጋዜጠኞች ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡

ስልጠናውን ከባህርዳር እና ሀዋሳ የመጡትን ጨምሮ በአጠቃላይ 66 የስፖርት ጋዜጠኞች የተከታተሉት ሲሆን፡ በአግባቡ ላጠናቀቁ 54 ጋዜጠኞች ደግሞ የአለም አቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር አለምአቀፍ ይዘት ያለው የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርም ለዚህ ስልጠና መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉትን አለምአቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርን፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን እና አዘማን ሆቴልን በማህበሩ አባላት ስም በማመስገን መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡

Please follow and like us:

በ ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም

የአለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) በየአራት አመቱ በሚያከናውነው የአለም ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ላይ አሸናፊ ለሆኑ ብሄራዊ ቡድኖች በሽልማት መልክ የሚሰጠው ዋንጫ (The FIFA World Cup Trophy) በመላው አለም ጉዞ እያደረገ ይገኛል፡፡

Continue reading

Please follow and like us:

 

በ  ቆንጂት ተሾመ 

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ውስጥ በአመራርነት ተወዳድራ ቦታ ማግኘት ችላለች። የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆነው ጋዜጠኛ ዮናስ ተሾመ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተወዳድሮ ኢትዮጵያ የመሪነት ቦታ አግኝታለች።

Continue reading

Please follow and like us:

በ አስፋው ስለሽ

የኮፓ ኮካኮላ ትምህርት ቤቶች ማጠቃለያ ውድድር በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወነ ይገኛል፡ ዘጠኝ ክልሎችና ሁለት የከተማ መስተዳደሮች እየተሳተፉበት ነው፡፡

ከሻምፒዮናው ጥሩ ብቃት ያሳዩ 79 ታዳጊዎች ወደ ኢትዮጵያ እና ጥሩነሽ ዲባባ ወጣቶች ስፖርት ማሰልጠኛ ማእከላት ለተሻለ ስልጠና ይገባሉ፡፡

Continue reading

Please follow and like us:

 

by Haileegziabher Adhanom

LONDON, AUGUST, 8, 2017 – With triple world and double 5000-10,000m Olympic champion Mo Farah saying goodbye to his beloved track, one of the questions raised by the eternal fans of distance races and the 10,000m in particular, is who is going to become the poster athlete, for an event on the verge of disappearance.

Continue reading

Please follow and like us:

 

 

By Abdu Mohamed

Ethiopian Flag Handover to Athlete Representatives. (Photo: Abdu Mohamed)

Addis Ababa, Aug 01,2017 – Ethiopian Athletics federation (EAF) officially see off its 40 selected athletes to represent Ethiopia in 13 different events for the upcoming London World Athletics Championship.

Continue reading

Please follow and like us:

በግርማቸው ከበደ

አዲስ አበባ ሀምሌ 22/2009 ዓ.ም – ከአንድ ሳምንት በኋላ በእንግሊዝ ለንደን የሚካሄደውን 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ምክንያት በማድረግ በወቅታዊ የአትሌቲክስ ጉዳዮች እና የዘገባ ጥራት ላይ ያተኮረው፤ በኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስፖንሰር በሆነው ሶፊ ማልት ትብብር የተዘጋጀው የአንድ ቀን የማነቃቂያ ስልጠና በስኬት ተጠናቋል፡፡ Continue reading

Please follow and like us:

በኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም

አዲስ አባባ፣ ሀምሌ 20/2009 ዓ.ም – ማህበራችን ከሀምሌ 28 እስከ ነሐሴ 07/2009 ዓ.ም በእንግሊዝ ለንደን የሚካሄደውን 16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ምክንያት በማድረግ አባላቱ በወቅታዊ የአለም አትሌቲክስ ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለመጨመር የሚያስችል የአንድ ቀን የማነቃቂያ ስልጠና የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 22/2009 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ጀምሮ በኢንተርኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል እንዳዘጋጀ አስታውቋል፡፡ Continue reading

Please follow and like us: