News

ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም፡ ቦነስ ኤየርስ – ጥቅምት 01/2011 ዓ.ም

በቦነስ ኤይረስ፡ አርጀንቲና እየተካሄደ በሚገኘው እና 5ኛ ቀኑን በያዘው የታዳጊዎች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች እየተካፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በጥሩ ሁኔታ ዝግጅቱን ሲያደርግ መቆየቱን የቡድኑ አባላት እንደሚከተለው ይገልጻሉ፡፡

አሰልጣኝ አብርሐም ኃ/ማርያም ” ረዘም ላለ ጊዜ ልምምድ መስራታችን፡ ቀደም ብለን ወደ ውድድሩ ቦታ መመምጣታችን ከልጆቹ በጥሩ አቋም መገኘት እና ጤናማ መሆን ጋር ተደምሮ ከፈጣሪ ጋር በውድድሩ ጥሩ ውጤት ለማምጣት እናስባለን”

አትሌት ሒሩት መሸሻ ” በጣም በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅተን ነው የመጣነው፡ እዚህ ከመጣን በሗላም ለውድድሩ የሚያግዙን ልምምዶችን ሰርተናል ከአየር ፀባዩም ጋር እየተለማመድን እንገኛለን፡ በአጠቃላይ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንገኛለንገኛለን”

በውድድሩ መርሀ ግብር መሠረት የኢትዮጵያ አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የተወሰኑ የቀጣይ ቀናት የውድድሮች ፕሮግራም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

✍ ሀሙስ ጥቅምት 01 ከምሽቱ 3:05 – የ3000ሜ ሴቶች የመጀመሪያ ዙር ፍጻሜ – አትሌት አበራሽ ምንስዎ

✍ ጥቅምት 01 ከምሽቱ 3:30 – የ3000ሜ ወንዶች የመጀመሪያ ዙር ፍጻሜ – በሪሁ አረጋዊ

✍ ጥቅምት 01 ከምሽቱ 4:20 – የ800ሜ ሴቶች የመጀመሪያ ዙር ፍጻሜ – አትሌት ሒሩት መሸሻ

✍ አርብ ጥቅምት 02 ከምሽቱ 2:30 – የ5000ሜ ሴቶች የርምጃ ውድድር ፍጻሜ- አትሌት ስንታየሁ ማሬ

✍ ጥቅምት 02 ከምሽቱ 3:10 – የወንዶች 2000ሜ መሠ. የመጀመሪያ ዙር ፍፃሜ – አትሌት አብርሀም ስሜ

✍ ጥቅምት 02 ከምሽቱ 3:25 – የሴቶች 2000ሜ መሠ. የመጀመሪያ ዙር ፍጻሜ – አትሌት መቅደስ አበበ

✍ ጥቅምት 02 ከምሽቱ 3:40 -የሴቶች 1500ሜ ማጣሪያ – አትሌት ለምለም ሀይሉ

✍ ጥቅምት 02 ከምሽቱ 4:00 – የወንዶች 1500ሜ ማጣሪያ – አትሌት መለሠ ንብረት

ማስታወሻ:- የታዳጊዎች ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ የውድድር ህግ ከ1500, 3000 እና 2000ሜ መሠናክል ውጭ ያሉት ውድድሮች የፍጻሜ ውድድር ሁለት ሁለት ጊዜ የሚከናወኑ ሲሆን በሁለቱም ውድድሮች በተመዘገቡ ሰአቶች በአማካይ የተሻላ ሰዓት ያመጡ አትሌቶች የአጠቃላይ አሸናፊ የሚሆኑ ሲሆን፡ ከላይ በተጠቀሱ የውድድር አይነቶች የሚሳተፉ አትሌቶች ደግሞ የመጀመሪያውን ዙር በነዚህ ውድድሮች ይሳተፉና ሁለተኛውን ዙር ደግሞ በ4 ኪ.ሜ የአገር አቋራጭ ውድድር የሚሳተፉ ሲሆን አሸናፊውን ለመለየት በተመሳሳይ የትራክ እና አገር አቋራጭ ውድድሮች የተመዘገቡት ሰአቶች አማካይ ውጤት የሚታይ ይሆናል፡፡

አለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ለዚህ ህግ መሻሻል ያስቀመጠው ምክንያት ታዳጊዎች ከቶሎ አሸናፊ መሆን ይልቅ ብርታት ላይ እንዲያተኩሩ በማሰብ ነው ያለ ሲሆን የአሸናፊው በአንድ የፍጻሜ ውድድር ብቻ አለመታወቅ ቅሬታ የፈጠረባቸውም አልጠፉም፡፡

Please follow and like us:

በ ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም – ቦነስአይረስ፡ መስከረም 26/2011 ዓ.ም

አራት ሽህ አትሌቶች፡ ከ206 ሀገራት በ32 የስፖርት አይነቶች ለ13 ቀናት፡ የአለምን ትኩረት በመሳብ አርጀንቲና በታሪኳ ያዘጋጀችው ትልቁን የስፖርት ውድድር ለማድመቅ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ይህችን ቀን ብቻ ይጠብቃሉ፡፡

Continue reading

Please follow and like us:

by Haileegziabher Adhanom, Secretary General, ESJA

ADDIS ABABA, July 25, 2018 – Ethiopian Athletics Federation (EAF) is targeting a much-improved result at the 21st African Athletics Championship in Asaba. Ethiopians disappointed at the previous championships in Durban, South Africa.

EAF Technical Director, Dube Jillo, told AIPS that, he firmly believes that Ethiopia will compete at the highest level for the ranks among Africa’s best talents in this championship. According to Mr. Dube, the EAF was going through an athletes and coaches selecting process to avoid previous grievances of the stakeholders at such events.

The EAF selected a very resilient squad that comprises young, talented and senior athletes, strong coaching staff with an amazing team spirit that will inevitably brought a huge success in the competition.

Moreover, it is the change of mentality in the athletes towards continental competitions that makes the technical director more and more optimistic about potential success in Asaba.

Ethiopia had an awful return of medals in Africa’s Biennial Athletics Championships two years ago. The Ethiopians came home with only six medals which included a single gold in the men’s 3000m steeplechase by Chala Bayou and two silver medals, resulting in eight spot on the continental ranking.

Besides that Ethiopia is a powerhouse in global athletics, the country has been a regular attendee and one of the challengers for top spot in this championships over the years, collecting 141 medals, among them 40 golds.

Superstars Genzebe Dibaba and Solomon Barega are some of the picks with a huge mission, among the 64-strong delegation accompanied by thirteen coaches, led by EAF Executive Committee member, Mr.Admasu Saji, to right the wrong that happened two years ago.

This year’s African athletics Championships will take place between August 1-5 at Asaba, Nigeria. The best Athletes in this competition will represent Africa at the IAAF’s Continental Cup in Ostrava next September.

Please follow and like us:

በ ግርማቸው ከበደ

የሁሉም አይኖች ላይ ጉጉት አለ፡፡ እየተያዩ ፈገግ ይላሉ፡፡ በዚህ ሳምንት የሚነግሱበትን ትራክ በእግሮቻቸው ነካ…ወጋ…እያደረጉ እንደገና ይስቃሉ፡፡ በእግሮቻቸው እና በትራኩ ንኪኪ የሚፈጠረው “ድምድምታን” እንደ ማጀቢያ ሙዚቃ እየተጠቀሙ ስለምቾቹ በደስታ ይወያያሉ፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የመጀመሪያ ልምምዳቸውን ሊሰሩ ታምፔሬ ስታድየም ተገኝተዋል፡፡ ይህ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ነው፡፡ አትሌቶቹ ወደ “ዋናው” ብሔራዊ ቡድን የሚሸጋገሩበት፡ “ሲኒየር” ከመሆናቸው በፊት ለዓለም አትሌቲክስ ራሳቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በወጣቶች ሻምፒዮና ራሱን ለዓለም ያስተዋወቀውን አለቃቸው ኃይሌ ገ/ስላሴን መመልከት ይበቃቸዋል፡፡

ይህ ግን አይጠፋባቸውም፡፡ ታምፐሬ የተገኙት ቀጣዩን ገፅ ለመግለጥ ነው፡፡ የታምፐሬ ስታድየምን ትራክ በእግራቸው እየፈተሹ የሚሳሳቁትም ለዛ ይሆናል፡፡ በድንገት ግን “ልምምዱን ሜዳ ላይ እንስራ!” የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ “አዎ…እሺ!”…

የፓርክ ልምምድ

ከስታድየም ወጥተው ሜዳ ፈለጉ፡፡ ደግነቱ ከስታድየሙ ውጭ ሜዳ አልጠፋም፡፡ በፕሃያርቪ ሃይቅ ዳር ባለ ጎዳና ሰውነታቸውን ማፍታታት ጀመሩ፡፡ የፓርኩ የጤና ሯጮች የኢትዮጵያ አትሌቶች በእነርሱ ጎዳና እያሟሟቁ እንደሆነ አውቀዋል፡፡ በበረራ የደከመ ሰውነትን ለማፍታት የተጀመረው ሩጫ ወደ ጠንካራ ልምምድ ተቀየረ፡፡ አሰልጣኞቹ “በቃችሁ!” ቢሉም ለጥቂት ደቂቃዎች ሰሚ አላገኙም ነበር፡፡ ወጣቶቹ በስሜት ተሞልተው ይለማመዳሉ፡፡ በታምፔሬ ለመንገስ ይተጋሉ፡፡

“አዲስ ትውልድ”

የ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ “ልጆቹ ጥሩ ስሜት ላይ ናቸው” ይላሉ፡፡ “እርስ በእርስም በደንብ ይግባባሉ፡፡”
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኃይሌ ወደ ኃላፊነት ከመጣ በኀላ በተደጋጋሚ የሚያነሳው ነገር “የብሔራዊ ቡድኑን ስሜት መመለስ” ነው፡፡ የወጣት ቡድኑ አንድነት ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ እንደሆነ ሻምበል ቶሎሳ ይናገራሉ፡፡ “አዲስ ትውልድ ናቸው፡፡ በቀላሉ መግባባት ይችላሉ” በማለትም ምክንያቱን ያስረዳሉ፡፡ በ5000ሜ ከሰለሞን ባረጋ ጋር ኢትዮጵያን የሚወክለው ጥላሁን ኃይሌም በአሰልጣኙ ሀሳብ ይስማማል፡፡ “ከብሔራዊ ቡድን ዉጪም ከብዙዎቹ ጋር አብረን ልምምድ እንሰራልን፡፡ ሻይ ቡናም እንላለን” ብሏል ከውድድሩ በፊት በአራራት ሆቴል በሰጠው ቃለ ምልልስ፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ ፕሬስ አታሼ ስለሺ ብስራትም “አንድነት እና ጠንካራ የማሸነፍ መንፈስ ያለበት ቡድን ነው” ይላል፡፡

በ “መሰናክል” መጀመር

ብሔራዊ ቡድኑ የታምፐሬ ፈተናውን በከባዱ ፈተና ጀምሯል-በሴቶች 3000ሜ መሰናክል፡፡ በውድድሩ የተሳተፉት ሁለቱም አትሌቶች ወደ ፍፃሜ አልፈዋል፡፡ በምድብ ሶስት የሮጠችው እታለማሁ ስንታየሁ ርቀቱን በ9:52.92 ደቂቃ በመጨረስ የራሷን ምርጥ ሰዓት አሻሽላለች፡፡
በምድብ ሁለት አገሬ በላቸው ለራሷ የዓመቱ ምርጥ ሰዓት በሆነ 9:59.95 በመሮጥ ለነገው ፍፃሜ አልፋለች፡፡

በ1500ሜ ወንዶች ማጣሪያ የኢትዮጵያ ከ20ዓመት በታች ሻምፒዮኑ ብርሃኑ ሶርሳ እና ውድድሩን እንደሚያሸንፍ በብዙዎች ግምት የተሰጠው ርቀቱ የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ሻምፒዮን ሳሙኤል ተፈራም ለሀሙሱ ፍፃሜ አልፈዋል፡፡

በ800 ሜትር ሴቶች ፍሬወይኒ ሀይሉ እና የርቀቱ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ውድድር አሸናፊዋ ድርቤ ወልተጂ ከየምድባቸው አንደኛ በመሆን የነገውን ግማሽ ፍፃሜ ፍልሚያ ይጠብቃሉ፡፡

በ20 ዓመት በታች ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በምትሳተፍበት የ400ሜ ውድድር በሴቶች ዛሬ በሚደረገው ማጣሪያ የርቀቱ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮኗ ፍሬህይወት ወንዴ እና ማህሌት ፍቅሬ ተሳታፊ ናቸው፡፡

የመጀመሪያዎቹ ፍፃሜዎች

5000ሜ ሴቶች ኢትዮጵያ ሜዳልያ ታገኝባቸዋለች ተብለው ከሚጠበቁት ርቀቶች አንዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የመጀመሪያው የፍፃሜ ውድድርም ይሆናል፡፡ ድንቅ የውድድር ዘመን እያሳለፈች የምትገኘው ግርማዊት ገብረ እግዚአብሔር ቅድሚያ ግምት አግኝታለች፡፡ ግርማዊት በ35ኛው የጃንሜዳ አገር አቋራጭ የ6ኪ.ሜ አሸናፊ ስትሆን የአፍሪካ አገር አቋራጭ የርቀቱ ሻምፒዮንም ናት፡፡ በአሰላ በተካሄደው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮናም የ5000ሜ ባለድል ነች፡፡ በአሰላው ውድድር ሁለተኛ የወጣችው እጅጋየሁ ታዬ ሌላኛዋ የ5000ሜ ተፈላሚ ናት፡፡ “እስካሁን የነበረው ዝግጅት በጣም ቆንጆ ነበር፡፡ ወርቅ እናመጣለን ብዬ እየጠበቅኩ ነው” ብላለች እጅጋየሁ፡፡

የወንዶች 10,000ሜ ፍፃሜም ዛሬ የሚደረግ ሲሆን በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ወርቅና ብር ያመጡት በሪሁ አረጋዊ እና ኦሊቃ አዱኛ ይፎካከራሉ፡፡ “ሰርተናል…ተዘጋጅተናል” ያለው በሪሁ” ከኦሊቃ ጋር ተባብረን አሪፍ ሩጫ እንሮጣለን” በማለት ስለዛሬው ፍፃሜ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በታምፐሬ ዶሃን ማለም

ከሁለት ዓመት በፊት በቢድጎሽ- ፖላንድ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ አራት የወርቅ፡ ሁለት ብር እና አራት ነሃስ ሜዳልያዎችን አሸንፋለች፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ የቴክኒክ መሪ ዱቤ ጅሎ ፌዴሬሽኑ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንዳቀደ አስታውቀዋል፡፡ ይህ ውድድር በሚቀጥለው አመት በዶሃ ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መሰረት እንደሚሆናቸው የተናገሩት አቶ ዱቤ አሁን በወጣት ቡድኑ ውስጥ ከሚገኙት አትሌቶች መካከል “80%ቱ የዓለም ሻምፒዮናው ላይ የሚታዩ” እንደሚሆኑም እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 

 

Please follow and like us:

በኦምና ታደለ

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር፣ ከአለምአቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር እና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር በትብብር ያዘጋጀው ስልጠና በሳምንቱ መጨረሻ ሚያዚያ 6 እና 7/2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዘማን ሆቴል ተካሂዷል፡፡ ስልጠናው በዋናነት በዘመናዊ የስፖርት ጋዜጠኛነት እና ፈተናዎቹ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡


በአዘማን ሆቴል የተካሄደውን ስልጠና የሰጡት የአለምአቀፉ የስፖርት ጋዜጨኞች ማህበር አስተማሪ እና ከ25 ዓመታት በላይ በስፖርት ጋዜጠኛነት ያሳለፉት ጣሊያናዊው ሪካርዶ ሮማኒ ሲሆኑ፡ ስልጠናው ጋዜጠኞች በዘመናዊው የሚዲያ አለም ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን በማመጣጠን እንዴት ማቅረብ እንደሚችሉ ተሞክሯቸውን በመጨመር ያካፈሉበት ነበር፡፡

በስልጠናው በተጨማሪም ጋዜጠኞች ለዜናዎች እና ትንታኔዎች በቂ ዝግጅት አድርጎ አግባብ የሆነ እና በፍሬ ነገር የተሞላ ዘገባ ማድረስ እንደሚቻል እንዲሁም በአንድ ግዜ ከአንድ በላይ ሙያዊ ክንዋኔዎችን እየሰሩ በዘመናዊው የሚዲያ አለም መላመድ እንደሚቻል ለማሳየት የተሞከረበት ስልጠና ለኢትዮጵያዊያን የስፖርት ጋዜጠኞች ተሰጥቷል፡፡ ሮማኒ በስልጠናው ላይ ዘመናዊ የስፖርት ጋዜጠኞች ከመፃፍ በዘለለ ፎቶዎች አና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ማንሳት እና ማረም ከጋዜጠኞች ዘመኑ የሚጠይቀው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የስፖርት ጋዜጠኝነት እና ስነ-ምግባር ሌላው በስልጠናው ላይ አፅኖት ተሰጥቶት ሰፊ ውይይት የተደረገበት ጉዳይ ነበር ፡፡ ስፖንሰርሺፕ፣ የፋይናንስ አቅም እና ፖለቲካ በብዛት ተፅዕኖ በሚያሳድሩበት የሚዲያ አለም ላይ የስፖርት ጋዜጠኞች ነፃ ለመሆን የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ላይ ስልጣና ተሰጥቷል፡፡
የአለምአቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር መሰል ስልጠና በኢትዮጵያ ሲሰጥ ይህ ለመጀመሪያ ሲሆን ፡ ቀጣይነት እንዲኖረውም በስልጠናው ተሳታፊ የነበሩ ጋዜጠኞች ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡

ስልጠናውን ከባህርዳር እና ሀዋሳ የመጡትን ጨምሮ በአጠቃላይ 66 የስፖርት ጋዜጠኞች የተከታተሉት ሲሆን፡ በአግባቡ ላጠናቀቁ 54 ጋዜጠኞች ደግሞ የአለም አቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር አለምአቀፍ ይዘት ያለው የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርም ለዚህ ስልጠና መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉትን አለምአቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርን፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን እና አዘማን ሆቴልን በማህበሩ አባላት ስም በማመስገን መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡

Please follow and like us:

በ ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም

የአለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) በየአራት አመቱ በሚያከናውነው የአለም ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ላይ አሸናፊ ለሆኑ ብሄራዊ ቡድኖች በሽልማት መልክ የሚሰጠው ዋንጫ (The FIFA World Cup Trophy) በመላው አለም ጉዞ እያደረገ ይገኛል፡፡

Continue reading

Please follow and like us:

 

በ  ቆንጂት ተሾመ 

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ውስጥ በአመራርነት ተወዳድራ ቦታ ማግኘት ችላለች። የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆነው ጋዜጠኛ ዮናስ ተሾመ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተወዳድሮ ኢትዮጵያ የመሪነት ቦታ አግኝታለች።

Continue reading

Please follow and like us:

በ አስፋው ስለሽ

የኮፓ ኮካኮላ ትምህርት ቤቶች ማጠቃለያ ውድድር በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወነ ይገኛል፡ ዘጠኝ ክልሎችና ሁለት የከተማ መስተዳደሮች እየተሳተፉበት ነው፡፡

ከሻምፒዮናው ጥሩ ብቃት ያሳዩ 79 ታዳጊዎች ወደ ኢትዮጵያ እና ጥሩነሽ ዲባባ ወጣቶች ስፖርት ማሰልጠኛ ማእከላት ለተሻለ ስልጠና ይገባሉ፡፡

Continue reading

Please follow and like us:

 

by Haileegziabher Adhanom

LONDON, AUGUST, 8, 2017 – With triple world and double 5000-10,000m Olympic champion Mo Farah saying goodbye to his beloved track, one of the questions raised by the eternal fans of distance races and the 10,000m in particular, is who is going to become the poster athlete, for an event on the verge of disappearance.

Continue reading

Please follow and like us:

 

 

By Abdu Mohamed

Ethiopian Flag Handover to Athlete Representatives. (Photo: Abdu Mohamed)

Addis Ababa, Aug 01,2017 – Ethiopian Athletics federation (EAF) officially see off its 40 selected athletes to represent Ethiopia in 13 different events for the upcoming London World Athletics Championship.

Continue reading

Please follow and like us: